ሳምንታዊ ጋዜጣ

ግብርና

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች  በ2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በበጋ መስኖ  ስንዴ ልማት ያገኘውን ምርት ለገበያ  ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ ፡፡

ኩባንያው በበጋ ወራት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በቆጂ ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ በበጋ መስኖ  ስንዴን በብዛት ለማምረት  ወደ ስራ መገባቱንና  ውጤቱም አበረታች እንደሆነ ገልፅዋል ፡፡

 ይህም በከተማዋ ብሎም በሃገሪቱ የሚስተዋለውን የምርት እጥረት ለመቀነስና  ገበያን  ለማረጋጋት እንደሚያግዝ የኩባንያው የግብርና ክፍል ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ጴጥሮስ ገልጸው  ድርጅቱ በ 2014 ዓ.ም በዞኑ ያመረተውን  ስንዴ ለመንግስት በሽያጭ መልክ ለማቅረብ  በሂደት ላይ መሆኑን አስረድተዋል።

 ዳይሬክተሩ አክለውም  በመጪው የክረምት ወቅት በወረዳው 350 ሄክታር ለማልማት መታቀዱን አስታውቀዋል። በተመሳሳይ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳጎሞቴ ወረዳ በ1 ሄክታር መሬት ላይ ሽንኩርት  በማልማት  200 ኩንታል ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን በአስቴር እርሻ ምንጠራ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል ።

 

የግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፍ

 ፐርፐዝብላክ ኢቲ.ኤች 20 የሚሆኑ የተለያዩ የዳቦ  ምርቶችን አምርቶ ለገበያ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ ፡፡

አድዋ ድልድይ አካባቢ በሚገኘው የዳቦ ማምረቻ  20 የሚሆኑ የተለያዩ የዳቦ  ምርቶችን አምርቶ በ አድዋ ሱቁ ለገበያ እያቀረበ ሲሆን እንደ በርበሬ፣ ሚጥሚጣ፣ ምስር እና የዳቦ ዱቄት ያሉ ለምግብነት የሚያገለግሉ ምርቶችንና ቅመማ ቅመሞችን  በማሸግ በሁሉም የከገበሬው ሱቆችና ለተለያዩ የመሸጫ መደብሮች ለሽያጭ እያቀረበ ይገኛል ፡፡  

የፐርፐዝብላክ ኢቲ.ኤች የግብርና ማቀነባበሪያ ዘርፍ የተለያዩ የግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመርና  በማቀነባበር ጥሬ እቃዎችን ለሃገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ በመላ ሃገሪቱ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለም ጭምር ነው ፡፡

 የፐርፐዝብላክ ምርቶችን ኤክስፖርት በማድረግ  የውጭ ምንዛሬ ግኝትን በማሳደግና የውጭ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት በሰነዶች እና በገበያ ስርአት ዙሪያ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በቀጣይም ሌሎች ግዙፍ የማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን ለመገንባት እቅዶችን በመንደፍ በእንቅስቃሴ ላይ ነው።

ከገበሬው ኢ ኮሜርስ

 ፐርፐዝብላክ ኢቲ.ኤች  የግብይት ስርዓቱን ለማዘመን የሚያስችል የሎጂስቲክስ ሥርዓት በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ ፡፡

ኩባንያው ደንበኞች በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ የሚፈልጉትን ምርትና አገልግሎት ኦንላይን ሆነው ሲያዝዙ በመረጡት ማድረሻ መንገድ ካሉበት ቦታ ለማድረስ የሚያስችል የሎጂስቲክ ሥርዓት በመዘርጋት ግብይትን በማሳለጥ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል ።

 በቅርቡ ተግባራዊ ከሚሆነው የቴሌ ብር የክፍያ መንገድ በተጨማሪ ደንበኞች  ሳይበርሶርስ፣ የኔ ፔይ እና  ፔይ ፓል ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም በመክፈል ያሻቸውን እንዲያዙ አስችሏል።

  ከገበሬው ኢ ኮሜርስ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ አምራቾች እና ገዢዎች በአንድ ቦታ የሚገናኙበት እና የሚገበያዩበት  ከገበሬው መተግበሪያን በማበልጸግ አገልግሎቱን በማዘመን የኩባንያውን ተደራሽነት አስፍቷል።

የከገበሬው የችርቻሮ መሸጫ መደብሮቻችን በሳምንቱ ከ 3 ሺ በላይ ሰዎች ማስተናገዱን አስታወቀ ፡፡

ፐርፐዝብላክ ኢቲ.ኤች በሳምንቱ በአዲስ አበባ ባሉት  በ 7ቱም ሱቆች አያሌ ቁጥር ያላቸው ደንበኞችን ማስተናገድ መቻሉን ያስታወቀ ሲሆን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ወላይታ ሶዶ አትክልትና ፍራፍሬ፣የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶችና ጥራት ያላቸው የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለኅብረተሰቡ በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝም ገልፅዋል።

  ከችርቻሮ መሸጫ መደብሮቻችን ባለፈ ለተለያዩ የንግድ ተቋማት እና መኖሪያ ቤቶች ጥራት ያላቸው  የግብርና ውጤቶችና የተቀነባበሩ ምርቶችን ማለትም አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳትና የእንስሳት ተዋጽዖ ምርቶችን እንዲሁም በርበሬ፣ ሚጥሚጣ ቅመማቅመሞችና መሰል ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ቀጥታ ከገበሬው እንዲኹም ከአምራቾች በመረከብ በተመጣጣኝ ዋጋ  ለኅብረተሰቡ እያደረሰ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

 

ልዩ ፕሮጀክቶች

የከገበሬው የተቀናጀ የግብርና ማስፋፊያ መርሐ ግብር (KIEP) የባለ አክሲዮኖቹን ቁጥር ከ 15 ሺ በላይ  ከፍ ማድረግ መቻሉን አስታወቀ ።

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ከሚያስተዳድራቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነውና ኩታ ገጠም እርሻ ያላቸውን ገበሬዎች ተጠቃሚ ለማድረግ በከገበሬው የተቀናጀ የግብርና ማስፋፊያ መርሐ ግብር (KIEP) የተመሠረተው የአክሲዮን ሥርዓት ያካተታቸውን ገበሬ ባለአክሲዮኖች ቁጥር 15 ሺ 601 ከፍ ማድረጉን አስታውቋል ።

በመላ አገሪቱ ሰባት ክልል ቢሮዎችን ከፍቶ ተደራሽ መሆን የቻለው ከገበሬው የተቀናጀ የግብርና ማስፋፊያ መርሐ ግብር (KIEP) የቅርንጫፍ ቢሮዎቹን ቁጥርም ወደ 12 ማሳደግ ችሏል። መርሐግብሩ 174 ሺ 826 አክሲዮኖች ምዝገባ(subscription) አካሒዶ 5 ሚሊዮን 224 ሺ 395 ብር በጥሬ ገንዘብ ሰብስቧል።

በአገር አቀፍ ደረጃ 1 ሚሊዮን ገበሬዎችን በኩታ ገጠም እርሻ ልማት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ምርት እንዲያመርቱና ለገበያ እንዲያቀርቡ ማስቻልን ዋና ዓላማው ያደረገው የከገበሬው የተቀናጀ የግብርና ማስፋፊያ መርሐ ግብር (KIEP) ተደራሽነቱን ለማስፋት እና በዕቅዱ መሠረት ገበሬዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትጋት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በመርሐግብሩ የሚካተቱት ባለአክሲዮን ገበሬዎች ያሏቸውን ኩታ ገጠም እርሻዎች በጋራ የሚያለሙበትን ውል ከፐርፐዝብላክ ጋር የሚዋዋሉ ሲሆን ከእርሻዎቻቸው የሚገኙትን ምርቶች ለኩባንያው በውሉ መሠረት በሽያጭ ሥርዓት እያስረከቡ ከዚያም ባለፈ ኩባንያው ከሚያገኘው አጠቃላይ ትርፍ ተከፋይ የሚሆኑበት ሒደት ተመቻችቷል።  

የአክሲዮኖች ሽያጭን የሚያመለክት  

Leave a Reply

4 × 5 =

×