ሴቶች ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬድንግ አክሲዮን ማኅበር ባመቻቸው የ‘ከገበሬው’ ምርት አከፋፋይ የሴቶች ፕሮግራም (KPDW) አባል በመሆን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀረበ

ሴቶች ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬድንግ አክሲዮን ማኅበር ባመቻቸው የ‘ከገበሬው’ ምርት አከፋፋይ የሴቶች ፕሮግራም (KPDW) አባል በመሆን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀረበ፡፡

ኩባንያው ከአዲስ አበባ የ5 ክፍለ-ከተሞች ነጋዴ ሴቶች ማኅበራት ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ያሰለጠናቸውን 120 ሴት ኢንተርፕርነሮችን በፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች የመሰብሰቢያ አዳራሽ አስመርቋል።

የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ያሰለጠናቸውን 120 ሴት ኢንተርፕርነሮችን በፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች የመሰብሰቢያ አዳራሽ አስመርቋል። በምረቃ ሥነስርዓቱ በክብር እንግድነት የተጋበዙት የፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬድንግ አክሲዮን ማኅበር መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ  ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ለምሩቃኑ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ሀገርንና ህዝብን የሚለውጥ ሀሳብ ይዞ በአነሳሽነት መነሳቱን ገልፀው ኩባንያው ከአመት በፊት ሲመሰረት በጥቂት ሰራተኞች ነገር ግን በግዙፍ ሀሳብ የተመሰረተ በመሆኑ ዛሬ ላይ 400 ሰራተኞች መቅጠሩንና በብዙ መልኩ በተግባር የሚታይ ለውጦች እያከናወነ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

አክለውም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ያመቻቸው ከገበሬው ምርት አከፋፋይ ሴቶች ፕሮጀክት እናቶችንና ሴት እህቶችን እንዲሁም ሸማቾችን  ለመጥቀም ያለመ መሆኑን ተናግረው በእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያና የኢጋድ አባል ሀገራት ነጋዴ ሴቶች ማህበራት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቱ ለምሩቃኑ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈው ተመራቂ ሴቶች ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬድንግ አክሲዮን ማኅበር ባመቻቸው መርሀ-ግብር ታቅፈው በመሥራት የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት የራሳቸውን አሻራ እንዲያኖሩ ጠይቀዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ታደለች በዚሁ ፕሮግራም ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች የነደፈው ፕሮግራም ለሴቶች ተጠቃሚነት የላቀ ፋይዳ ያለው ስለሆነ አብሮ ለመሥራት አስፈላጊውን ሁሉ እንፈፅማለን ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ካምፓኒው ለማኅበራቱ ስለ ፕሮግራሙ (KPDW) አጠቃላይ ሁኔታ ገለፃ በመስጠት አብሮ ለመሥራት የሚሆን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ከኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ጋር  የስምምነት ሰነድ የተፈረመ ሲሆን ለምሩቃኑ ሰርተፍኬት በመስጠት ተጠናቋል።

Leave a Reply

14 + 3 =

×