ተደራራቢ ልዮ ፍላጎት ያላቸው ህፃናት ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲጠበቁ ማድረግ ይገባል በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች : ህፃናትና ማህበራዊ ጎዳይ ቢሮ: ትኩረት ለሴቶች እና ህፃናት ማህበር እና ኢትዮ ሀበሻ መስማት የተሳናቸው ኪነጥበብ ማህበር ጋር በመተባበር በአፍሪካ ለ 32ኛና በኢትዮጵያ ለ31ኛ ጊዜ የአፍሪካ ህፃናት ቀን በፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል።
በሁነቱ ላይ የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጎዳይ ቢሮ ተወካይ የአፍሪካ ህፃናት ቀን ሲከበር ምንም አይነት ችግር የሌለባቸውን ህፃናትን ብቻ ሳይሆን ልዮ ፍላጎት ያላቸውና ተደራራቢ ችግር ያለባቸው ህፃናትን ጭምር ማሰብ አስፈላጊ መሆኑን በማመን በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግና አስፈላጊነቱን ለማስረፅ መርሀግብሩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
ልዮ ፍላጎት ያላቸው ታዳጊ ህፃናት ከግንዛቤ ማነስ የተነሳ በየቤቱ በር ተቆልፎባቸውና የሚገባቸውን ያህል ትኩረት ሳይሰጣቸው ማየት ለህሊናችን ቁስል ሊሆንብን ይገባል ያሉት የትኩረት ለህፃናት መስራች ሲስተር አሳየች በበዓላት ብቻ ሳይሆን በየእለት እንቅስቃሴችን ልናስባቸው ይገባል።
ትኩረት ለህፃናት በ15 ዓመታት ቆይታው በበርካታ ነገሮች ላይ በዋናነት ደግሞ ሴቶች ላይ ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው አሁን ላይ ልዮ ፍላጎት ያለባቸው ህፃናት ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል ሲስተር አሳየች።
ሲስተር አሳየነች አክለውም ልዮ ፍላጎት ያላቸውን ህፃናት ገንዘብ መስጠት ባንችል እውቀት አልያም ደግሞ ምንም የማያስከፈለውን ፍቅር እንስጥ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በስራቸው ለተባበርዎየው ባለድርሻ አካላትና መርሀ ግብሩ እንዲከናወን አዳራሽ ለፈቀደው ፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች ከልብ ምስጋና ይድረስልኝ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሁነቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ልጆችን ማየት በራሱ በብዙ መልኩ የሀገርን ተስፋ ማየት ነው ተስፋችን ደግሞ ልዮ ፍላጎት ያላቸው ብቻ ሳይሆኑ በልዮነት ልዮ ፍላጎት የሚሹ ናቸው ምክንያቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ ሀሳብ ይዘው በፈጠራ ስራቸው የሰዎችን ህይወት ያቀለሉ የሀሳብ ባለቤቶች ልዮ ፍላጎት ያስፈልጋቸዋል የተባሉት ናቸው።
በመሆኑም ልዮ ፍላጎት የሚሹ ልጆቻችንን ከምንም በላይ ፍቅርና እንክብካቤ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።
ዶ/ር ፍሰሃ አክለውም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች የኑሮ ውድነትን ማቅለል ብቻ ሳይሆን የስራ እድል መፍጠር ላይ እንደሚያተኩርና የቢዝነስ ተቋም ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ እንደሚሳተፍ ገልፀው ሴቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ፕሮጀክት በኩባንያው መጀመሩን አብስረዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ኢትዮ ሀበሻ መስማት የተሳናቸው ኪነ ጥበብ ማህበር የባህል ብድን ውዝዋዜና ኪነ ጥበባዊ ስራዎቻቸውን ያቀረብ ሲሆን የጥያቄና መልስ ውድድርም ተካሂዷል።
ከሰኔ 8,2014ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ለ31ኛ ጊዜ የአፍሪካ ህፃናት ቀን እየተከበረ ይገኛል።
Leave a Reply