የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ቺፍ ሪቴል ዲስትሪቢዩሽን ኦፊሰር የከገበሬው ሪቴል መደብሮችን የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ከሠራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄዱ።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የከገበሬው ሪቴል መደብሮቹን በተመለከተ እስከአሁን ድረስ ያለውን የሥራ እንቅሰቃሴ በመገምገም በቀጣይ ይበልጥ ውጤታማ ሊያደርገው የሚችለውን ውይይት ቺፍ ሪቴል ዲስትሪቢዩሽን ኦፊሰር ወ/ሮ ሰናይት አየለ፣ አሲስታንት ሪቴል ዲስትሪቢዩሽን ኦፊሰር አቶ አሳየኸኝ እሸቱ እና  የከገበሬው መደብር ሁሉም ቅርንጫፎች የተገኙ ሠራተኞች በተገኙበት ተከናውኗል።

በውይይቱ ንግግር ያደረጉት የሪቲል ቺፍ ዲስትሪቢዩሽን ኦፊሰር ወ/ሮ ሰናይት አየለ፤ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የተዳለች ሆና ከሌሎች ዓለም ሀገራት በተለየ ደሀ  የሆነችው እኛ ጠንካራ ሠራተኛ አለመሆናችን የሚያመላክት መሆኑን ገልፀው  ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የከገበሬው መደብሮችን የከፈተበት ዋና ዓላማ በጋራ ተባብሮ በመስራት ቀጥታ ከገበሬው የሚረከበውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማች ማህበረሰብ ለማድረስ በመሆኑ  ዓላማውን ለማሳካት የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል ፡፡

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያን በርካታ እናቶችና አባቶች  ዓላማው ገዝቷቸው ካላቸው ላይ ቆንጥረው ያቋቋሙት ድርጅት መሆኑን የጠቀሱት አሲስታንት ሪቴል ዲስትሪቢዩሽን ኦፊሰር አቶ አሳየኸኝ እሸቱ፤ ኩባንያው በአዲስ አበባ ከተማ በከፈታቸው ሁሉም የከገበሬው መደብር ቅርንጫፎች የሚሠሩ ሠራተኞች ጠንክረው በመስራት ለውጤታማነቱ ጉልህ ሚና መጫወት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ተያይዞም የከገበሬው መደብሮች በቀጣይ ለደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችላቸው ከዚህ ቀደም ይጠቀሙባቸው የነበሩትን የቴል ብር ሽያጭ አገልግሎት ጨምሮ ሌሎች ፈጣንና የተቀልጣፉ አገልግሎቶች መስጠቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልፆል።

ሪፖርተር፦ ናታን ታደለ

 

Leave a Reply

three × five =

×