የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ በንግድና ስራ ፈጠራ ዘርፍ ዕጩ ተሸላሚ ሆኑ!

የበጎ ሰው ሽልማት ዘንድሮ በዘጠኝ ዘርፎች በሚያከናወነው መርሃ ግብር የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱን ለኢኮኖሚያዊ ብልፅግና እያደረጉ ላሉት አስተዋፅኦ በንግድና ስራ ፈጠራ ዘርፍ ለሽልማት አጭቷቸዋል ፡፡
ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የግል ዮኒቨርስቲ በማቋቋምና ለትምህርት ጥራት የበኩላቸውን በመወጣት በሀገሪቱ የግል ዮኒቨርስቲዎች መበራከት መሰረት የጣሉም ናቸው ፡፡
ዶ/ር ፍሰሃ በአሜሪካን ሀገር በነበራቸው ቆይታ ጥቁር ህዝቦች ላይ በሚደረገው ስርዓት አልባ ምጣኔ ሀብታዊ መገለልና መድሎ እንዲሁም የሀብት መባከን ቁጭት ሳቢያ ለአመታት ሲያወርዱና ሲያወጡ የነበረውን ሀሳብ ለኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ብሎም ለኢትዮጵያ ወዳጆች በማጋራት የበርካቶችን ቀልብ የገዛና ትኩረት የሳበውን ብላክ ኢኮኖሚ ኤክሰለንስ ( የጥቁር ህዝቦች ምጣኔ ሀብታዊ ልህቀት ) በሚል ራዕይ ሰንቀው ወደ ስራ መግባታቸዉ የተግባር ሰው መሆናቸውን አስመሰክሮላቸዋል፡፡
ዶ/ር ፍሰሃ ምንም እንኳ በቀደመው ስርዓት በነበረው ተፅዕኖ ከሀገር ለቀው የወጡ ቢሆንም የወገን መቸገርና የሀገር ኢኮኖሚያዊ አቅም ቁልቁል መውረድ እረፍት ከነሳቸው ጥቂት ኢትዮጵያዊያን አሳቢዎች መካከል ናቸውና ከተደላደለ የውጪ ሀገር ኑሮአቸው ሀገር መለወጥ ፣ ትውልድ መገንባትና ወገንን መታደግ በሚል ልበ ቀና ፤ እሩቅ አሳቢ ኢትዮጵያዊያንን በማሰባሰብ የጥቁር ህዝቦች ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ጅማሬው የነፃነት ቀንዲል ተምሳሌት፣ የጥቁር ህዝቦች መከታና ፣ የሰው ዘር መገኛ በሆነችው ትውልድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ላይ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር በሚል ዛሬ ላይ የሀገር ለውጥ ይመለከተናል የሚሉ ከ 4 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ባለአክሲዮኖችን ያሳተፈ ኩባንያ መመስረታቸው ሀገር ወዳድነታቸውን የሚያመላክት ነው፡፡
ዶ/ር ፍሰሃ በመላው አለም የሚገኙ ጥቁር ህዝቦች የላቀ ምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ እንዲያመጡ ካስፈለገ ጥቁር ህዝቦች በዋናነት የሚተዳደሩበት ዘርፍን በመለየት ወደ ስራ መግባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ በግብርና ላይ ትኩረት በማድረግና ሌሎች ተያያዝ ዘርፎች ላይ ማለትም የግብርና ማቀነባበር ፣ ሪቴል እንዲሁም ኢ-ኮሜርስ ላይ የሚሰራ ኩባንያ ሲመሰርቱ በርካቶችን በማሳተፍ ሲሆን ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች አንድ አመት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ ከ 400 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ኩባንያም ሆንዋል ፡፡
በተጨማሪም አቅማቸው የደከመ የማህበረሰብ ክፍሎችን በኢኮኖሚ ለመደገፍና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ለማድረግ ሃሽታግ ኖሞር ሀንገር በሚባል እና እንዲሁም በሌሎች አቅዶ እየተገበራቸዉ ባሉ የተለያዮ ፕሮጀክቶቹ እየሰራ የሚገኝ ኩባንያም ነው ፡፡
በመሆኑም በበጎ ሰው ሽልማት ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ እጩ ሆነዉ የቀረቡት ለኢኮኖሚ ብልፅግና እያደረጉ ላሉት አስተዋፅኦ በንግድና በስራ ፈጣሪነት መሆኑ ተመላክቷል ፡፡
ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች
ኮሙዮኒኬሽን ዲፓርትመንት
ኑ አብረን እንስራ !!

Leave a Reply

5 × three =

×