የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ አንዱ አካል የሆነው #NoMoreHunger ፕሮጀክት ከNMH EVENT እና MEDIA ጋር በመተባበር ለአንድ መቶ ሀያ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው መስከረም 12 2015 ዓ.ም በፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነው የተሰጠው። 

 ከፐርፐዝ ብላክ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት በፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የ#NoMore Hunger ግሎባል ኤቨንትስ ዳይሬክተር  ወ/ሪት ፍሬህይወት ጌታቸው ሰልጣኞቹ የተመለመሉት በማህበራዊ ሚዲያ መሆኑን ገልጸው፤ የስልጠናው ዋና ዓላማ በ#NoMoreHunger ስር ያሉ 1st Annual Great Global ጨምሮ በሌሎች ዲፓርትመንቶች ላይ ብዙ የሰው ሀይል የሚያስፈልግ በመሆኑ እና ስለፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ግንዛቤ ማስጨበጥ ዋነኛ ግቡ ማድረጉን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ሰልጠኞቹ በኩባንያው ለመስራት በሚሰማሩበት ወቅት ተገቢ የሆነ የስራ ስነ -ምግባር እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነጥቦች እንደተነሱ ወ/ሪት ፍሬህይወት ገልፀዋል። 

ከ15 ቀን በኋላ 2ተኛ ዙር ስልጠና እንደሚኖር እና ሰልጣኞቹ በመረጡት ክፍል ስራን እንደሚጀምሩ ያስታወቁት ዳይሬክተሯ፤ ስራውን  በሚሰሩበት ወቅት የሚያሳዩት ውጤት እና የስራ ስነምግባር ታይቶ በድርጅቱ ቋሚ ሆነው የሚቀጠሩበትን ዕድል ኩባንያው እንደሚያመቻች ነው ያስታወቁት።

 

ዳይሬክተሯ አያይዘውም ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ በችግር ላይ ለሚገኙ ወጎኖች ገቢ ማሰባሰቢያ ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚያከናውነው የሩጫ ውድድር ቅድመ ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ ገልጸው፤ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንዲሁም ድርጅቶች የበኩላቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የ #NoMoreHunger ፕሮጀክት ዓላማ በተለያየ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘላቂ የሆነ ኢኮኖሚ መፍትሄ  በመስጠት ሀገራችንና ወገናችንን ከተመፅዋችነት ማላቀቅ መሆኑን ይታወቃል። 

ፕሮጄክቱ በመጀመርያው ሁለት ዓመታት ዉስጥ 50,000 በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሚሊየነርነት መቀየር ላይ ያተኮረ ነዉ።

ሪፖርተር፦ ህይወት ከሊል

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ RISK MANAGEMENTን በተመለከተ ለኩባንያው ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ስልጠና ሰጠ።

ለፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት ሥልጠናውን የሰጡት RISK MANAGEMENT ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አቶ ሁሴን  ናቸው።

የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ሜክሲኮ ሰንጋተራ በሚገኘው ዋና መስሪያቤት የዋና ሥራ አስፈፃሚው የመሰብሰቢያ አዳራሽ  ውስጥ ለሁለት ግማሽ ቀን በተሰጠው ስልጠና ዋነኛ ትኩረቱን በእርሻ፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ሪቴል ፍራንቻይዝ ሼር ሆልደር ሞዴል እና የከገበሬው የኦላይን የመገበያያን ጨምሮ በሌሎች በርካታ ዘርፎች እየሠራ የሚገኘው ኩባንያው

 በሠው ሀይል አስተዳደር ብሎም በሌሎች የሙያ መስኮች በሚያከናውናቸው እያንዳንዱ የሥራ እንቅስቃሴዎቹ ላይ ቅድመ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን በጥልቀት መመርመር እንደሚገባ በመድረኩ ተነግሯል።

ሪስክ ወይም አደጋን ሙሉ በሙሉ መቅረፍ  አይቻለም ያሉት አቶ ሁሴን ፤ ነገር ግን በየዕለት ተዕለት ለምናካሂዳቸው የሥራ እንቅስቃሴዎቻችን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ከቻለን  የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች መቀነስ ስለሚያስችለን ለውጤታማነታችን ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

መርሀ ግብሩ አመራሮች ባነሱት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጎባቸው ሥልጠናው ተጠናቋል።

መሰል ሥልጠናዎች በቀጣይ ጊዜያትም እንደሚቀጥሉ ተገልፆል።

ሪፖርተር፦ ናታን ታደለ

Leave a Reply

four × 1 =

×