ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች በአጋርነት የተሳተፈበት 2ተኛው የአርሲ ገበሬዎች ፌስቲቫል ተካሄደ።
ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ በአጋርነት የተሳተፈበት 2ኛው የአርሲ ገበሬዎች ፌስቲቫል ግንቦት 14 2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በቆጂ ከተማ የፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ፣ የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሙሳ ፉሮ እና ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው የተካሄደው።
ፐርፐዝብላክ ሚዲያ ያነጋገራቸው የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ በፌስቲቫሉ በመሳተፋቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀው ፌስቲቫሉ በአካባቢው ለሚገኙ ገበሬዎች እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ እና አዳዲስ ነገሮችን በአንድ ቦታ ለማግኘት እድል ይፈጥራል ብለዋል።
በቀጣይ በሚካሄዱ ፌስቲቫሎች ላይ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች በተሻለ መልኩ ውጤታማ ስራዎችን ይዞ እንሚቀርብም ገልፀዋል።
የ2ተኛው የአርሲ ገበሬዎች ፌስቲቫል አዘጋጅ ጋዜጠኛ አንዱዓለም ጌታቸው በበኩሉ የፌስቲቫሉ ዋና ዓላማ አርሲ ዞን ላይ የሚገኙ ገበሬዎችን በማዝናናት እና በማስተማር እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ ለማድረግ መሆኑን በመናገር፤ ከዚሁ አንፃር በዕለቱ የተካሄደው ፌስቲቫል የታቀደለትን ዓላማ ማሳካቱንም ገልፀዋል።
ወደፊትም ፌስቲቫሉ ቀጣይነት እንደሚኖረው የተገለፀ ሲሆን በሀገር በቀል እውቀት የተሠሩ ምርቶች ለህብረተሰቡ እንደሚያቀርቡም ተነግሯል።
በመድረኩ ለ2ኛው የአርሲ ገበሬዎች ፌስቲቫል መሳካት እገዛ ላደረጉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የእውቅና ስነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የሰርተፍኬት እና ዋንጫ ስጦታ ተበርክቶለታል።
በዕለቱ በአንድ ኩንታል ገብስ የተሰራው ግዙፍ ገንፎ ለዕይታ ቀርቧል።
በህይወት ከሊል
ግንቦት 14/ 2014ዓ.ም
Leave a Reply