ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች በደቡብ ክልል አርባምንጭ ከተማ ያስገነባውን የአርባምንጭ የተቀናጀ የባህላዊ ምግቦች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ስራ መጀመሩ ተነገረ።

ፐርፐዝብላክ ሚዲያ በስፍራው ተገኝቶ ያነጋገራቸው የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የቴክኒካል ክፍል ዋና ሀላፊ እንዲሁም የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዲፓርትመንት ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር ሽመልስ አድማሱ ኩባንያው በደቡብ ክልል አርባምንጭ ከተማ ሼቻ ክፍለከተማ በ4መቶ አምስት ካሬ ሜትር የገነባነውን ፋብሪካ በአጭር ግዜ ውስጥ ትርፋማ ለማድረግ እየሰሩ እንደሚገኙ ነው የገለፁት።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የህዝብ ፍላጎት ማዕከል አድርጎ የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን ያስታወሱት ፕ/ር ሽመልስ አድማሱ በፋብሪካው ለሚሰሩ ሰራተኞች ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር አኳያ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አከናውነው ወደ ስራ መግባታቸውንም ተናግረዋል።

የፋብሪካው የማምረት አቅምን በተመለከተ እቅድ አውጥተው እየሰሩ መሆናቸውን የገለፁት ዳይሬክተሩ በምርቶች አቅርቦት ዙሪያም እጥረት እንዳይከሰት ከኩባንያው የማርኬቲንግ ዲፓርትመንት ጋር አብረን እንሰራለን ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም ኩባንያው ምርት ከማምረት ባሻገር ጥሬ ዕቃዎችን ለመሰል አምራች ፋብሪካዎች እንደሚያቀርቡም አስታውቀዋል።

የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች የአርባምንጭ የባህላዊ ምግቦች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የሂሳብ ባለሙያ የሆነችው ወ/ት ባምላክ ተሻለ ኩባንያው በአርባምንጭ ከተማ የገነባው ፋብሪካ በከተማዋ ለሚኖሩ ወጣቶች ትልቅ የስራ ዕድልን እንደፈጠረላቸው በመግለፅ፤ ኩባንያው ይዞት የተነሳው ዓላማ ፍሬያማ እንዲሆን የበኩሏን አስተዋፅኦ እንድምታደርግ ቃል ገብታለች።

የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዲፓርትመንት ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር ሽመልስ አድማሱ ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ የተስማሚነት እና ምዘና ድርጅት እውቅና ስርተፍኬት ያገኘው የአርባምንጭ የተቀናጀ የባህላዊ ምግቦች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ አሁን ላይ ከደቡብ ክልል እንዲሁም ከጋሞ ዞን የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንዲያገኝ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ገልፀው፤ በቀጣይ ፋብሪካው የሚያመርታቸውን ምርቶች የሚያከፋፍልበት የእራሱ መደብር እንደሚኖረውም አስታወቀዋል።

የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የአርባምንጭ የተቀናጀ የባህላዊ ምግቦች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሽሮ እና በርበሬን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የባልትና ውጤቶችን እንደሚያመርት ዋና ዳይሬክተሩ ፕ/ር ሽመልስ አድማሱ ገልፀዋል።

ናታን ታደለ
ሰኔ11/2014 ዓ.ም

Leave a Reply

eleven − 10 =

×