ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ በዋና መስሪያ ቤቱ የግብርና ምርቶች ሽያጭ ማቅረቡን አስታወቀ።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከከፈታቸው ስድስት የሪቴል ሱቆች እና የሞባይል ትራኮች በተጨማሪ ተደራሽነቱን ለማሳፋት በማሰብ ሜክሲኮ ሰንጋተራ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ሽያጭ መጀመሩን የሀሳቡ አመንጪ እና የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የከገበሬው መደብር አድዋ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ወ/ት ትዕግስት አስመላሽ ለፐርፐዝብላክ ሚዲያ ገልፀዋል።

በስፍራውም ሽንኩርት፣ ቲማቲም እና ድንችን ጨምሮ በርከት ያሉ የግብርና ምርቶች ስለሚገኙ ሁሉም ሰው የፈለገውን ምርት መጥቶ መገብየት እንደሚችል አስታውቀዋል።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ዋነኛ ዓላማው ህብረተሰቡ የተሻለ ኑሮ እንዲኖር ማድረግ በመሆኑ ከሱቆቹ በተጨማሪ ለማንኛውም ሸማች የሚፈልገውን ምርት ያለበት ስፍራ የማድረስ አገልግሎት እንደሚሰጡም ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በሀገራችን የትኛውም ድርጅት በዋና መስሪያ ቤቱ መሰል ሽያጭ ሲያካሄድ እንዳልነበር እና ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች የመጀመሪያው መሆኑን የገለፁት ወ/ት ትዕግስት በቀጣይ በከገበሬው መደብር አድዋ ቅርንጫፍ የተጀመረው የዳቦ እና የፈጣን ምግቦች አቅርቦት ፕሮጀክትን እናስመርቃለን ብለዋል።

የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የከገበሬው መደብር አድዋ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ት ትዕግስት አስመላሽ በዓይነቱ አዲስ የሆነውን ሀሳብ አምነው እና ተቀብለው በአጭር ጊዜ ተግባራዊ እንዲሆን ላገዟቸው የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ እንዲሁም ለሌሎች ለኩባንያው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ናታን ታደለ
ሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

Leave a Reply

three × 3 =

×