ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ አዲስ የቀጠራቸው ሰራተኞቹ ወደ ስራ ሲገቡ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ስልጠና ሰጠ።

ኩባንያው በቅርቡ በሚከፍታቸው 6የሪቴል ሱቆች ውስጥ እንዲሰሩ የቀጠራቸውን በተለያየ የሙያ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ከ15 በላይ ሰራተኞቹን በተቋሙ የሰው ሀይል አስተዳደር ሀላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ማሞ አና የበርካታ ሙያ ባለቤት በሆኑት ወ/ሮ የኔአለም ታዬ አማካኝነት የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ስልጠና ሰጥተዋል። በስልጠናው በቅድሚያ ንግግር ያደረጉት የኩባንያው የሰው ሀይል አስተዳዳር ሀላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ማሞ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ኢትዮጵያ ውስጥ ሰርቶ መለወጥ አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ ለመቀየር ትኩረቱን በግብርና ላይ በማድረግ ቁርጠኛ ሆኖ እየሰራ የሚገኝ ድርጅት በመሆኑ አዚህ የተገኛችሁ ሰራተኞች ራሳችሁን ለዚህ ትልቅ ዓላማ ብቁ አድርጋችሁ መገኘት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

ሀላፊዋ አክለውም ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ እያንዳንዳችን በኢኮኖሚ የተሻለ ደረጃ ላይ እንድንገኝ ለማስቻል ትልቅ ዓላማ ይዞ የተነሳ ኩባንያ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ በሁሉም የሙያ መስክ የምተሰማሩ ሰራተኞች ይህን ሀላፊነት በአግባቡ እንድትወጡ ሲሉም ሰልጣኞችን ጠይቀዋል። ሌላው ተቋሙ ባዘጋጀው የስልጠና ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ለአዳዲስ የተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና የሰጡት ወ/ሮ የኔዓለም ታዬ በበኩላቸው እንደ ሀገር በሀያላን ሀገራት የሚደርስብን ጫና ከድህነታችን የሚመነጭ ነው፤ በመሆኑም ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ለዚህ ትልቅ ችግር ዘለቄታዊ መፍትሄ ለማበጀት የተመሰረተ ድርጅት በመሆኑ በእኔነት ስሜት ደስተኛ ሆናችሁ ልትሰሩ ይገባል ሲሉ ተቋሙን ለተቀላቀሉት አዳዲስ ሰራተኞች ንግግር አድርገዋል።

Leave a Reply

twenty + 3 =

×