ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጋር በመተባበር የከገበሬው ምርት አከፋፋይ ፕሮጀክትን አስመልክቶ ከወጣቶች ጋር ተወያያ።

ፐርፐዝብላክ ኢቲዮጵያ የስራ ፈላጊ ወጣቶችን እና ሴቶች ግንዛቤ ፈጠራ እና ገበያ ማረጋጋት ፕሮግራም “የወጣቶች እና ሴቶችን ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን” በሚል መሪቃል ባሳለፍነው ሳምንት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኦፍ ስታፍ አቶ ተፈራ ሀይሉ፣የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉነህ ፈይሳ ፤ እንዲሁም ሌሎች የኩባንያው የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ውይይት ተድርጓል፡፡

በውይይቱ ንግግር ያደረጉት የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኦፍ ስታፍ አቶ ተፈራ ሀይሉ ፐርፐዝብላክ በከገበሬው ምርት አከፋፋይ ወጣቶች ፕሮጀክት 11 ሺህ ወጣቶችን አሳትፎ ተጠቃሚ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸው፤ ወጣቶቹ ኩባንያው ከገበሬው ቀጥታ ተረክቦ የሚያቀርብላቸውን የግብርና ምርት በአካባቢያቸው ለሚገኙ ሸማች ህብረተሰብ ክፍሎች ባሉበት ድረስ እንዲያቀርቡ ለማድረግ እና በፕሮጀክት ለወጣቶች የስራ ዕድልን ከመፍጠር  ባለፈ በአሁኑ ወቅት እየናረ የመጣውን የኑሮ ውድነት የማረጋጋት ስራ ለመስራት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የከገበሬው ምርት አከፋፋይ ወጣቶች ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ጌታቸው በበኩላቸው በፕሮጀክቱ የስራ ዕድል የሚያገኙ ወጣቶች በመጀመሪያ ያለምንም ቅድመ ክፍያ የ5000 ብር የከገበሬው ምርት እንደሚቀርብላቸው አንስተው ወጣቶቹ በርትተው  መስራት ከተቻሉ ደግሞ የምርት አቅርቦቱን ከፍ እንዲል ያደርገዋል ነው ያሉት።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የወጣቶች እና ስፖርት  ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተከተል በበኩላቸው በሀገራችን በርካታ የስራ ዕድል የሚፈልጉ ወጣቶች እንዳሉ አስታውሰው፤ ከፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ወጣቶች ወደ ስራ የሚገቡበትን ዕድል እንደተመቻቸ ያስታወቁ ሲሆኑ፤ ወጣቶቹ በፕሮጀክቱ በንቃት በመሳተፍ ውጤታማነታቸውን እንዲያስመሰክሩ ጠይቀዋል፡፡

ሪፖርተር፦ ህይወት ከሊል

 

Leave a Reply

seven + eight =

×