ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ከጪንቻ ደጋ ፍራፍሬ ግብይት ሁለገብ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ጋር አብሮ ለመስራት መስማማቱ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ዘውዴ እና ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች የስትራቴጂክ ፕላኒንግ እና የቢዝነስ ዴቭሎፕመንት ዳይሬክቶሬት ስር የቅርንጫፍ ቢሮዎች ሀላፊ የሆኑት አቶ ሰማኸኝ ደሳለኝ ሰኔ1ቀን 2014ዓ.ም በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን ጪንቻ ከተማ ተገኝተው ከጪንቻ ደጋ ፍራፍሬ ግብይት ሁለገብ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አሰኔ ጋር ከተወያዩ በኃላ ነው።
በውይይቱም የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ዘውዴ ፐርፐዝብላክ እንደ ድርጅት አብሮ ሰርቶ መለወጥ እንችላለን የሚል ፅኑ እምነት ያለው መሆኑን ተናግረው በጪንቻ አካባቢ ለሚገኙ አርሶአደሮች የገበያ እድል ከመፍጠር በተጨማሪ በርከት ያለ ምርት ማምረት እንዲችሉ አስፈላጊውን የቴክኖሎጂ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቋል።

በጪንቻ ከተማ የሚገኙ አርሶአደሮች ከአፕል በተጨማሪ ጥቅልጎመን እና ካሮትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የአትክልት ምርቶችን በብዛት የሚያመርቱ መሆናቸውን የገልፁት የጪንቻ ደጋ ፍራፍሬ ግብይት ሁለገብ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አሰኔ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ለአርሶአደሩ ማህበረሰብ የተሻለ የገበያ አማራጭ ስለሚፈጥር ከኩባንያው ጋር በጋራ ለመስራት መሉ በሙሉ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በደቡብ ክልል የጋሞ ዞን የምትገኘው የጪንቻ ከተማ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ1943 ዓ.ም ጀምሮ የአፕል ምርትን ማምረት እንደጀመረች የጪንቻ ደጋ ፍራፍሬ ግብይት ሁለገብ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ፀሀፊ አቶ ጉንጆ ዳልጌ ገልፀዋል።

ናታን ታደለ
ሰኔ11/2014ዓ.ም

Leave a Reply

19 − fifteen =

×