ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የከገበሬው ምርት ስርጭት አገልግሎትን በተመለከተ ሀገር ውስጥ ካሉ የግብርና ምርት አምራቾች እና አቅራቢዎች ጋር ተወያየ።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች በኢትዮጵያ እንመግብ ፕሮጀክቱ ለሸማቹ ህብረተሰብ የግብርና ምርቶችን በየመኖሪያ ቤቱ ለማቅረብ በሚያስችለው የገበሬው ምርት ስርጭት አገልግሎት ዙሪያ ሀገር ውስጥ ካሉ የግብርና ምርት አምራቾች እና አቅራቢዎች ጋር ሜክሲኮ ሰንጋተራ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የውይይት መርሀ ግብር አካሂዷል፡፡

በውይይቱ የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሀ እሸቱ፣ የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ቺፍ ኦፍ ስታፍ አቶ ተፈራ ሀይሉ፣ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ቺፍ ቴክኒካል ኦፕሬሽን ኦፈሰር ወ/ሮ ፍሬህይወት ገብረህይወት እንዲሁም የከገበሬው የተቀናጀ ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር አቶ አስናቀ ሀ/ሚካኤል እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ ለእንግዶቹ ስለአገልግሎቱ ገለፃ ያደረጉት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ፤ የከገበሬው ምርት ስርጭት አገልግሎት ዋነኛ ዓላማው ሸማቹ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ምርት ጊዜውን፣ ገንዘቡን እና ጉልበቱን በቆጠበ መልኩ በቅናሽ ዋጋ በየመኖሪያ ቤቱ ማቅረብ መሆኑን ተናግረዋል።

አገልግልቱ ለግብርና ምርት አምራቾች እና አቅራቢዎችም ከደንበኞቻቸው ጋር በቀላሉ መገናኘት የሚችሉበትን ሥርዓት እንደሚፈጥርላቸውም ዋናሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

ፐርፐዝብላክ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ እንደመሆኑ ምቹ የገበያ ስርዓትን ለመፍጠር ይሰራል ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ የከገበሬው ምርት ሥርጭት አገልግሎት የግብርና ምርት አምራቾች እና አቅራቢዎች በዋነኝነት ትኩረታቸውን ምርትን በበቂ ሁኔታ ማቅረብ ላይ
ሥርዓቱ ለግብርና ምርት አምራቾች እና አቅራቢዎች የገንዘብ ዕጥረት ችግርን እንደሚቀርፍ ነው የገለፁት።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ሥራ በጀመረ በዓመት ከሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ከ 5000 በላይ ባለአክሲዮኖች እንዲሁም ከ800 በላይ ሠራተኞች እንዳሉት ያስታወሱት ዶ/ር ፍሰሀ ፤ ኩባንያው ማንኛውም ሸማች ህብረተሰብ የሚፈልገውን ምርት ያለበት ስፍራ ድረስ በብድር ማግኘት የሚችልበትን ሥርዓት እየዘረጋ በመሆኑ ፐርፐዝብላክ ምርቶችን ለሸማቹ ህብረተሰብ የሚያቀርብበትን ዋጋ የሚወስኑት እራሳቸው አምራቾቹ እና አቅራቢዎቹ መሆናቸውንም አስታወቀዋል።

የገበሬው ምርት ስርጭት አገልግሎት በቀጣይ ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እንደሚጀምር ይፋ ተደርጓል።

የውይይት መርሀ ግብሩ በዕለቱ ከተገኙ ያቄዎች የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ምላሽ ተሰጥቶባቸው ተጠናቋል።

 

Leave a Reply

7 − 2 =

×