ለፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት ሥልጠናውን የሰጡት RISK MANAGEMENT ዲፓርትመንት ዳይሬክተር አቶ ሁሴን ናቸው።
የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ሜክሲኮ ሰንጋተራ በሚገኘው ዋና መስሪያቤት የዋና ሥራ አስፈፃሚው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለሁለት ግማሽ ቀን በተሰጠው ስልጠና ዋነኛ ትኩረቱን በእርሻ፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ሪቴል ፍራንቻይዝ ሼር ሆልደር ሞዴል እና የከገበሬው የኦላይን የመገበያያን ጨምሮ በሌሎች በርካታ ዘርፎች እየሠራ የሚገኘው ኩባንያው
በሠው ሀይል አስተዳደር ብሎም በሌሎች የሙያ መስኮች በሚያከናውናቸው እያንዳንዱ የሥራ እንቅስቃሴዎቹ ላይ ቅድመ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን በጥልቀት መመርመር እንደሚገባ በመድረኩ ተነግሯል።
ሪስክ ወይም አደጋን ሙሉ በሙሉ መቅረፍ አይቻለም ያሉት አቶ ሁሴን ፤ ነገር ግን በየዕለት ተዕለት ለምናካሂዳቸው የሥራ እንቅስቃሴዎቻችን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ከቻለን የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች መቀነስ ስለሚያስችለን ለውጤታማነታችን ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።
መርሀ ግብሩ አመራሮች ባነሱት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጎባቸው ሥልጠናው ተጠናቋል።
መሰል ሥልጠናዎች በቀጣይ ጊዜያትም እንደሚቀጥሉ ተገልፆል።
ሪፖርተር፦ ናታን ታደለ
Leave a Reply