ፐርፐዝብላክ ኢቲ.ኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከገበሬው የተቀናጀ ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙ ከሂዶታ እና ኢሲፔ ዲቻ ዮኒየኖች ጋር ነው የተፈራረመው፡፡
ስምምነቱ የተፈረመው አንድ ሚሊዮን ገበሬዎችን ባለአክሲዮን በማድረግ የኩባንያው ባለቤት እንዲሆኑ እያመቻቸ በሚገኘው ከገበሬው የተቀናጀ ኤክስቴንሽን ፕሮግራሙ ሲሆን የስምምት ሰነዱ መርሃ ግብር ለሀገር አንድነትና ለስራዎች ስኬት በሚል በህሊና ፀሎት ተጀምሯል ፡፡
መርሃ ግብሩን በንግግር የጀመሩት የፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች ቺፍ ሰፖርት ኦፕሬሽንሽ ኦፌሰር ወ/ሮ ሶፌያ ነጋሽ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች በ ኢትዮጵያ ሲመሰረት በዋናነት ከእለት እለት እየተወደደ በመጣው የኑሮ ውድነት ሳቢያ ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን የአብዛኞችን ህይወት ለመለወጥና ቀጥታ ምርትን ከገበሬው ለሸማች በማድረስ ከእርሻ ወደ ጉርሻ መርህን ይዞ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡
አክለውም ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ይህንን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ አብሮ መስራት የማይተካ ሚና እንዳለው በማመን የስራ አጋር መሆን ከሚችሉና ፍላጎት ካሳዮ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ እየተፈራረመ ይገኛል ብለዋል ፡፡
በመሆኑም በእለቱ ከሂዶታና ከኢሲፔ ዲቻ ዮኒየኖች ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም በመገኘታችን ሁላችንም እንኳን ደስ አለን በማለት ፕሮግራሙን አስጀምረዋል ፡፡
ከገበሬው የተቀናጀ ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ አስናቀ ሀ/ሚካዔል በበኩላቸው ከገበሬው የተቀናጀ ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ከማንም በላይ ገበሬው እንዲከበር ለማድረግ ፣ በኢኮኖሚ እንዲጎለብት ማድረግ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው ፕሮግራሙ አንድ ሚሊዮን ገበሬዎችን የኩባያችን ባለቤት የማድረግ ዉጥን ይዞ የተነሳ ስለመሆኑም አስረድተዋል ፡፡
ከገበሬው የተቀናጀ ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በሀገሪቱ በ11 ክልሎችና በ2ቱም ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንና 1 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ ከ 1ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ፣ ከገበሬው ማይክሮ ፋይናንስ ኩባንያ ና ከገበሬው ኢንሹራንስ ኩባንያ በመመስረት እንዲሁም ከገበሬው ምርት መሰብሰቢያና ምርት ማሰራጫ ቦታዎችን በማደራጀት ተመጣጣኝ በሆነ የአገልግሎት ክፍያ የብድር አገልግሎት እዲያገኙ ማስቻል ፣ የኢንሹራስ አገልግሎት መስጠት ፣ ገበሬውን የሚደግፍ የግብርና ግብዓችን ማሟላት ፣ አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም የመካናይዜሽን አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል ፣ የተመረተው ምርት ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለሸማቹ እንዲደርስ ማስቻል በጥቅሉ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታውን ማረጋጋት ላይ ዓላማዉን ያደረገ መሆኑን አስረድተው ከዮኒየኖቹ ጋር በጋራ የሚሰራው ስራም ይህንኑ ያማከለ ነው ብለዋል ፡፡
ዋና መቀመጫውን በአዉሮፓ ያደረገው የስራ ሀላፌ አቶ ብሩክ በበኩላቸው ድርጅታቸው ከፐርፐዝብላክ ጋር አብሮ ለመስራት የስምምነት ስነድ ሲፈራረም አንድ የሚያደርገው የጋራ አላማ ስላለው መሆኑን ተናግረው ኑሩ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በተለያዮ የአለም አካባቢዎች ርሃብን ለማጥፋት በግብርና ፣ በጤና ፣ በትምህርት እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎቶች ላይ የሚሰራ መሆኑን ገልፀው ሀገር ስትለወጥ ዜጎች ኑሯቸው ሲሻሻል ለማየት በመጀመሪያ ግብርናና ገበሬው ላይ መስራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን እኛም የምናምንበት በመሆኑ በጋራ ለመስራት ብቻ ሳይሆን ገበሬ ጭምር ለመሆን መነሳታቸውን በቆራጥነት አብራርተዋል ፡፡
በ2008 ዓ.ም ተመስርቶ በ 8 ወረዳ ላይ 65 መሰረታዊ ማህበራትን ማፍራት የቻለው ሂዶታ ዮኒየን ሰብሳቢ አቶ ከበደ ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች በመነሻነት እየሰራበት ያለው ሀሳብ ፈጣሪ ድሆችን ተመልክቷል የሚያሰኝ ጭምር ነው ብለዋል በመሆኑም እርሳቸውን ጨምሮ በ65 መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት ውስጥ የታቀፉ አርሶ አደሮች የእኔም ገበሬ ነኝ አባል እንደሚሆኑ ቃል እገባለው ብለዋል ፡፡
በሌላ በኩል ኢሴፔ ዲቻ ስራ አስከያጅ በበኩላቸው የዮኒየኑ መጠሪያ የአማርኛው ፍቺ በአንድ ላይ ማደግ መሆኑን ተናግረው ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነው ኩባንያው በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ያለውን አጠቃላይ አደረጃጀት አድንቀዋል ፡፡
የሀገር እድገትና የኢኮኖሚ ብልፅግና የሚገኘው ሰሪው የልፋቱን ዋጋ ሲያገኝና አምራች የሚባለው የማህበረሰብ ክፍል ደግሞ ጠግቦ ሲያድር ነውና ጆንያ ያለ እህል እንደማይቆመው ሁሉ የሀገር እድገትና የኢኮኖሚ ብልፅግና ያለ ገበሬው የሚታሰብ ፤ ሳይለፋ የሰው ላብ በእጥፍ የሚወስደው ደላላ ሳይጠራ የሚሳካ ባለመሆኑ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ያሉት የአቅርቦት ሰንሰለት ቺፍ ወ/ሮ ፍሬህይወት ናቸው ፡፡
በመርሃ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች የቦርድ አባልና የህግ አማካሪ ዶ/ር ኤርሚያስ በበኩላቸው በህብረት ስራ ዮኒየኖች የሚመረተውን በቆሎ ሙሉ በሙሉ እንደሚረከቡ ቃል ገብተው በጋራ በመስራተቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል ፡፡
አብሮ መስራት ፣ የገበሬውን ሀገር በቀል እውቀት መጠቀምና ምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ ለማምጣት መሰረት ነው ያሉት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች የቦርድ አባል ወ/ሮ ሚሊዮን ወልደፃዲቅ ኑ አብረን እንስራ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
መርሀግብሩም የህብረት ስራ ዩኒየኖቹ ከፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ በመፈራረም ተጠናቋል ፡፡
Leave a Reply