ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ከገበሬው ምርት አከፋፋይ-ሴቶች ፕሮጀክትን ይፋ አደረገ

በመርሀግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች አ.ማ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጨቆነ ሳይሆን የተከበረ ጥቁር ማህበረሰብ ለማየት ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ማምጣት አማራጭ የሌለው ጎዳይ መሆኑን በማመን የተነሳ ኩባንያ ነው ብለዋል። ቀደምት አባቶቻችን ትውልድ ለማዳንና የተከበረች ሀገር ለመገንባት የደምና የላብ ዋጋ ከፍለው በታላቅ ወኔ ድል አድርገው ሉዓላዊት ሀገር ያቆዮልን በሀሳብ: በልዕልናና በክብር የሚኖር ትውልድን ለማፍራት ጭምር እንጂ በኑሮ ውድነት ተሽመድምዶ ሀሳብና ልቡ የሚዋልል በተዘዋዋሪ መንገድ ቅኝ ተገዚ የሆነ ትውል ለመፍጠር አለመሆኑን ማሰብ አለብን ብለዋል።

በመሆኑም ዛሬ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ሲነሳ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት የተላቀቀ በራሱና በሀገሩ የሚተማመንና የተከበረ ትውልድ ለማየት መሆኑን ተናግረው ይህ ሲታሰብ ግን ያለ ግብርናና ፀሀይ እያቃጠላቸው ልጅ አስተምረው በርካታ ሙያተኞችን ያፈሩ እንስፍስፍ ባለውለታ እናቶችና ሴቶች ፍፁም የሚታሰብ አይደለምና የከገበሬው ምርት አከፋፋይ -ሴቶች ፕሮጀክት እዚሁ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው ብለዋል። ዛሬ ላይ እርስ በእርስ በማጨራረስ እያፋጀን ባለው የኑሮ ውድነት ችግር ላይ ሌላ አካል ሳንጠብቅ በጋራ በስራ መዝመት ብንችል ከማንም በተሻለ ውጤታማና ታላቅ ህዝቦች እንሆናለን ለዚህ ደግሞ እንደ ፐርፐዝብላክ አይነት ተቆርቋሪ ሀሳብ ያላቸው የግል ተቋማት አስፈላጊነታቸው የሚያጠያይቅ አይደለም ያሉት. አቶ ዳኜ ክፍለ ከተማው በሚያስፈልገው ሁሉ ከጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል።
ገበሬውም ሆነ ሸማቹ ማህበረሰብ በተላይም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ባለውለታ እናቶችና ሴቶች ከቀን ወደ ቀን ኑሯቸውና የእለት ገቢያቸው እየተሸማቀቃቸው ፀሀይ እያቀጠላቸውና በክረምት ዝናብና ብርድ እያንገላታቸው የልፋታቸውን ዋጋ የማያገኙትን እናቶችና ሴቶች የጎሊት ነጋዴዎች መደገፍ አማራጭ የሌለው ጎዳይ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሃ እሸቱ ናቸው።

በሀገራችን ላይ እያገጠመን ባለው የሸቀጦች ዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ችግር የወጣቶችን ሰርቶ የመለወጥ ተስፋን ያላሸቀና ብዙዎችን ጎዳና ላይ ያወጣ መሆኑን የተናገሩት ኢ/ር…. ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ከገበሬው ምርት አከፋፋይ ሴቶች ፕሮጀክት ለሴቶችና ለእናቶቻችን ብቻ ሳይሆን ለወጣቶችና ለመላው ማህበረሰብ የተስፋ ጭላንጭል ጭምር ያሳየ መሆኑን ገልፀው በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ውስጥ ከፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ጋር የኑሮ ውድነት ችግራችንን እንደምንቀርፍ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ ብለዋል።

ቀደምት አባቶቻችን ሀገር ሉዓላዊነትዋ ተከብሮ እንዲቀጥል ያደረጉት ከእናቶች ምርቃትን ከሚስቶች እና ከእህቶች ደግሞ ስንቅ ይዘው በመዝመት ነበር እና
ዛሬ ደግሞ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች አዳማጭ ያጡ ትን እና በኢኮኖሚ የተደቆሱ ትን እናቶችና እህቶችን ፈልጎ በማነጋገር የመፍትሄውን አንድ እርምጃ በመውሰዳችሁ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ የእናቶችና የአባቶች ፀሎት አይለያችሁ ያሉት በመድረኩ ላይ የተገኙትና በፕሮጀክቱ የታቀፉት እናት ወ/ሮ ሙሉ ናቸው።
በመጨረሻም
በመድረኩ ላይ በፕሮጀክቱ ውስጥ ለተካተቱ እናቶች: ሴቶች እና ወጣቶችም መታወቂያና የስራ መለዮ ልብስ ተሰጥቷቸዋል።

 

Leave a Reply

12 − two =

×