ዓለም አቀፍ ፈንድ ርሃብን ለማስወገድ የተሰኘው ፕሮጀክት በዘንድሮው ዓመት ለዘላቂ ማህበረሰብ ልማት በሚል በገጠርማ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኝ የገበሬውን መንደር የተሟላ የመሰረተ ልማት አቅርቦት እንዲኖረው ማስቻል ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡
ፕሮጀክቱ አንድ ሚሊዮን አርሶ አደሮችን ባለአክሲዮን ለማድረግ እየተደረገ ካለው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የሚካሄድ ሲሆን በሚቀጥሉት 3 ዓመታት 5 ሚሊዮን ሰዎችን ከድህነት ለማውጣት በራዕይ አስቀምጦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቱ 1 ቢሊዮን ዶላር በዓመት በማሰባሰብ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ለትርፍ የተቋቋሙ የቢዝነስ ድርጅቶች እንዲሁም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተጠቁሟል ፡፡
በሰላማዊት ደበበ
Leave a Reply