ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች የባህላዊ ምግቦች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ።

የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች የአግሮ ፕሮሰስ ዲፓርትመንት ሀላፊ የሆኑት ፕ/ሮ ሽመልስ አድማሱ ተቋሙ በአርባምንጭ ከተማ የባህላዊ ምግቦች ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ሴቻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደሚገነባ ገልፀዋል። ከፐርፐዝብላክ ሚዲያ ጋር ቆይታ ያደረጉት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች የአግሮፕሮሰሲንግ ዲፓርትመንት ሀላፊ የሆኑት ፕ/ሮ ሽመልስ አድማሱ ዲፓርትመንታቸው በርካታ ዕቅዶች እንዳሉት በመግለፅ አሁን ላይ በዋነኝነት ጥራታቸውን የጠበቁ የባህላዊ ምግቦች ማቀነባበሪያ ፋብሪካን በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ በተለምዶ ሴቻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለመገንባት የሚያስችለውን አስፈላጊውን ቅድመዝግጅት በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ሀላፊው አክለውም እንደተቋም በአግሮፕሮሰሲንጉ ዘርፍ ትልቅ ውጤት ለማምጣት አቅደው ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች ጋ በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ እና ለተግባራዊነቱም ተገቢውን ክትትል አያደረግን እንገኛለን ሲሉ ለፐርፐዝብላክ ሚዲያ ተናግረዋል። ከ14 በላይ ፋብሪካዎችን በደቡብ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ ለመገንባት አቅዶ ወደ ስራ የገበው የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች አግሮ ፕሮሰሲንግ ዲፓርትመንት ዕወቀቱ፣ ችሎታው እና አቅሙ ያላቸው ወጣቶችን አካቶ በመስራት ላይ አንደሚገኙም ጨምረው ገልፀዋል። ሀላፊው አያይዘውም በኢትዮጵያ ብቻ መገኛውን ያደረገው የጅላዳ ዝንጀሮን የዲፓርትመንታቸው የስያሜ መጠሪያ እንዳደረጉት እና ይህም የያዙትን ዓላማ ከማሳካት ምንም እንደማይበግራቸው ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። የጋሞ ዞን አስተዳደር ስራቸው ውጤታማ እንዲሆን አያደረገላቸው ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ፕ/ሮ ሽመልስ አድማሱ ከፐርፐዝብላክ ጋ አብሮ መስራት ሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ መንግስታዊ እና መንግታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ባላቸው አቅም በጋራ ሰርተን ሀገራችን ኢትዮጵያን እንለውጥ የሚል ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Leave a Reply

4 × four =

×