ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ግምታዊ ዋጋው 60 ቢሊዮን ብር የሆነ ግዙፍ ህንፃ ሊገነባ መሆኑን ይፋ አደረገ ።
በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ :በአፍሪካ እንዲሁም በሀገርአቀፍ ደረጃ ደግሞ ትልቁን የከገበሬው ህንፃ/ታወር እንደሚሆን ተገልጿል ።
ዓለም አቀፍ የገበሬው የምስጋና ታወር በተለይም ገበሬውን እናመሰግናለን የምንልበት ራሳችንን በኢኮኖሚ እያበለፀግን ለሰዎች የምንደርስበት ነው ተብሏል።
ታወሩ 20ሺ ስኩዌር ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን በጥቅሉ 6 ህንፃዎችን አካቷል።
115 ፎቅ ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትመንት: ባለ 50 ፎቅ የፐርፐዝብላክ ዋና መስሪያ ቤትና ማዕከል: ባለ 50ፎቅ ሆቴል: ባለ 50 ፎቅ ለቢሮና ለሱቅ አገልግሎት የሚውሉ: ባለ 50 ፎቅ ለመዝናኛና የተለያዮ የመሰብሰቢያ አዳራሾች : ከመሬት በታች 5 ፎሎር ፓርኪንግ ያካተተ ግዙፍ ህንፃ መሆኑ ተገልጿል።
መርሀ ግብሩን በህሊና ፀሎት ያስጀመሩት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ የገበሬው ምስጋና ታወር በተላይም በኢትዮጵያ የገንዘብ አያያዝ ሁኔታን እንዲሁም እርዳታን ወደ ኢንቨስትመንት በመለወጥ ርሃብን መዋጋት የሚሉትን መሰረታዊ ሀሳቦች መነሻ እንደሆኑት በመግለፅ ኢንቨስት በማድረግ ለብዙዎች መድረስ የምንችልበት ልዩ የሆነ ፕሮጀክት በመሆኑ ሁሉም ሰው ተሳታፊ ይሁን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ህንፃው እ.አ.አ በ 2026 ጥር ላይ ለማጠናቀቅ በእቅድ ተይዞ እየተሰራ ነውም ተብሏል።
የፕሮጀክቱ አባል መሆን የሚፈልጉ ግለሰቦች :ማህበራት: ኩባንያዎች: የሀገር ውስጥና የውጪ ኢንቨስተሮች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን በቅድሚያ ግን ለኢትዮጵያዊያን ቅድሚያ ተሰጥቷል ተብሏል።
የዚህ ታሪክ ባለቤት ለመሆን የሚፈልጉና በ ሁለት ወር ውስጥ ኢንቨስት በማድረግ ሀገር ለመለወጥ ቆርጠው ለተነሱ የራዕይው ተጋሪዎች ቅናሽ እንዳለው ዶ/ር ፍስሃ ገልፀዋል።
ከ 30 ሚሊዮንና ከዛ በላይ ኢንቨስት በማድረግ የከገበሬው ህንፃ/ታወር ባለአክሲዮን ለሚሆኑ ሁሉ ባለ 4 መኝታ ቤት የመኖሪያ ቤት አፓርታማ : እንዲሁም ከ 55 ሚሊዮን በላይ ኢንቨስት ለሚያደርጎ ደግሞ 450 ካሬ ላይ ያረፈ ቅንጡ አፓርታማ በነፃ የሚያገኙ መሆኑም በመርሀግብሩ ተጠቅሷል።
የከገበሬው ታወር ኢንቨስተሮች ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች በተሰማራባቸው ዘርፎች በሙሉ የባለቤትነት ድርሻ እንደሚኖራቸውም ተገልጿል።
በመርሀ ግብሩ በርካቶች ባለቤት ለመሆን ፍላጎት ሲያሳዮ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰዎች ደግሞ ተመዝግበዋል።
ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት
Leave a Reply