ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች 7ተኛውን የሪቴል ፍራንቻይዝ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከፈተ።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ለሪቴል ፍራንቻይዝ ሼር ሆልደር ሞዴሉ 7ተኛውን የከገበሬው መደብር ቅርንጫፍ በወላይታ ሶዶ ከተማ መክፈቱን አስታወቀ።

በመርሀግብሩ ላይ የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ቺፍ ቴክኒካል ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ ታደለ ሰይፉ፣ የኩባንያው የግብርና ዲፓርትመንት ዋና ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ጴጥሮስ እንዲሁም የወላይታ ሶዶ ከተማ የንግድ እና ገበያ ልማት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍሰሀ ፀጋዬ እና ሌሎች የኩባንያው ሠራተኞች ተገኝተዋል።

የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ከገበሬው መደብሮች ኩባንያው ከገበሬው በቀጥታ ተቀብሎ የሚያመጣቸውን የግብርና ምርቶች በቅናሽ ዋጋ ለሸማቹ ህብረተሰብ የሚያቀርብበት እንደሆነ ይታወቃል።

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ መጋቢት 10 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያዎቹን 6 የገበሬው ሪቴል መደብሮችን ማስመረቁ ይታወሳል።

ሪፖርተር፦ ናታን ታደለ

 

  

Leave a Reply

nineteen + two =

×