በጋሞ ዞን ከ2350 ጫማ ከፍታ በላይ በምትገኘው የዶርዜ አማራና ኦዶ መንደር በፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ አስተባባሪነት ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ስፍራው አቅንተው የነበሩት ዲያስፖራዎች እና የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ቱሪዝምን ለማስፋፋት እና ለአካባቢው ህዝብ የመጠጥ ውሀ የማጎልብት ሥራ በማከናወን፤ ለማህበረሰቡ ንፁህ የመጠጥ ውሀ ለማድረስ ቃል በገቡት መሰረት የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ስፍራው ያቀናው የፐርፐዝብላክ ጋዜጠኞች እና የኮምኒኬሽን ቡድን አባላት ያገሩን በሬ በሀገሩ ሰርዶ ነውና ያለባቸውን ችግር ለመረዳት በዶርዜ አማራና ቦዶ መንደር ከሚገኙ የሀይማኖት አባቶች፣መምህራኖች እና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ስለማህበረሰቡ ችግር በስፋት ተነጋግረዋል። በስፍራው የተገኙትና ከዶርዜ ከተማ ነዋሪ አቶ ጩባሮ ጩቾ የዶርዜ ማህበረሰብ ከአንድ መቶ ሺህ እንደሚበልጥ ተናግረው በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ባለው የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ችግር እና በሌሎች በርካታ የመሰረተ ልማት ጉድለቶች በመኖራቸው መክኒያት የዶርዜ ማህበረሰብ ረጅም ግዜ ከኖረበት ስፍራ ወደ ሌላ አካባቢ እየተሰደደ ስለሚገኝ በአፋጣኝ መፍትሔ እንዲበጅላቸው ጠይቀዋል ፡፡ በዚሁ የውይይት ሰነሰርአት ላይ፤ በአንፃሩ የዶርዜ ማህበረሰብ የዕለት ጉርሱን ለማግኘት ለረጅም ዓመታት በርካታ ኪሎ ሜትሮችን እቃ ተሽከሞ በእግሩ ለመጓዝ በመገደዱ ለበርካታ ችግሮች ሲጋለጥ መቆየቱን ያስታወሰው በዶርዜ መንደር የአማራና ቦዶ አለቃ አቶ ታረቀኝ ቦጋለ ጩርቦ ፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ ዶርዜ ኢኮሎጅ በሚል ስያሜ አንድ መቶ ሀያ አምስት ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች በሸክላ፣ በጥጥ ፈተላ፣ ሽመናን ጨምሮ በሌሎች ሞያዎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ተናግሯል፡፡
ከዚሁ ጋር በተገናኘ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት ያደረጉት የፐርፐብላክ ኢቲኤች የኮምኒኬሽን እና የጋዜጠኞች ቡድን አባላት፤ ወደ ዶርዜ መንደር የመጡት፤ ለነዋሪው ንፁህ የመጠጥ ውሀ ከማቅረብ በተጨማሪ የረጅም ዓመት ባህል፣ ማንነት እና ታሪክ ያለውን የዶርዜ ማህበረሰብን ማስተዋወቅ ዓላማቸው መሆኑንም የኩባንያው የኮምኒኬሽን ሀላፊ አቶ ተፈራ ሀይሉ በስፍራው ለተገኙት የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቋል። የብሉ ማትሪክስ ኮንሰልታንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢንያም ሙላቱ በበኩላቸው የማህበረሰቡን የመጠጥ ውሃ የማጎልብት ሥራ ለማከናወን የገባነውን ቃል በተግባር ለምተርጎም በስፍራው መገኘታቸውን በመግለፅ፤ የዶርዜ ማህበረሰብ በአንድነቱ እና በጠንካራ የስራ ባህሉ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ህብረተሰብ እንደመሆኑ በቀጣይ አብረን ሰርተን የናንተን ህልም፣ የእኛን ፍላጎት ዳር እንዳርሰዋለን ሲል ተናግሯል። በስፍራው የተገኘው የፐርፐዝብላክ ሚዲያ ያነጋገራቸው የውይይቱ ተሳታፊዎችም ለረጅም ግዜ የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት በማጣታቸው ህፃናት ልጆችን ጨምሮ ከብቶቻቸው ላይ ትልቅ ጉዳት ሲያደርስባቸው መቆየቱን አስታውሰው፤ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ይህን ችግር ለመቅረፍ በመምጣቱ ከፍተኛ የደስታ ስሜት እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል። በቀጣይም አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ጨምረው አስታውቀዋል። ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የዶርዜ መንደር ማህበረሰብ ንፁህ የመጠጥ ውሀ እንዲያገኝ አስቦ መሀንዲሶችን በመምጣቱ በአካባቢው ሽማግሌዎች ተመርቋል፣ ከፍ ያለ ምስጋናም ቀርቦለታል።
Leave a Reply