ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጭ ሀገር መቀመጫቸውን ያደረጉ ተቋማት በGlobal summit against hunger እና በGreat Global Run ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ።

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጲያ በጥር ወር 2015 ዓ.ም በሚያካሂደው የGlobal summit against hunger እና Great Global run ላይ በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጭ ሀገር የሚገኙ ተቋማት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።

በጉባኤው በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ከ2000 በላይ ተሳታፊዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልፆል።

Global fund Against hunger እና Great Global Run የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ #NoMoreHunger ፕሮጀክት አካል መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤
የፕሮጀክቶቹ ዓላማ ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ከተሞች ባጋጠሙ የተፈጥሮ እና ሠው ሠራሽ አደጋዎች ሳቢያ ለረሀብ እና ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን ዓለም ላይ የሚገኙ ዜጎችን እንዲሁም ተቋማትን በማስተባበር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያገኙ የማድረግ ዓላማ እንዳለው የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ መግለፃቸው ይታወሳል።

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የሚያዘጋጀው የመጀመሪያው Global Summit Against Hunger ጥር 8 እና 9 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ ከዋና ሥራ አስፈጻሚው ቢሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ምርትን ከገበሬው በቀጥታ ተቀብሎ ለሸማቹ ህብረተሰብ በማድረስ በሀገሪቱ ውስጥ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ሪፖርተር፦ ናታን ታደለ

 

 

Leave a Reply

eighteen + nineteen =

×