ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ባለሞያዎች ማህበር ጋር በጋር ለመስራት የሚያስችለውን የስራ መግባቢያ ስምምነት ሰነደ ተፈራረመ፡፡

ፐርፐዝብላክ ኢትኤች ትሬዲንግ አ.ማ ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ባለሞያዎች ማህበር ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን የስራ መግባቢያ ስምምነት ሰነደ ባሳለፍነው ሳምንት የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሸሀ እሸቱ እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ባለሞያዎች ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር መንግስቱ ከተማ በተገኙበት ነው የተፈራረሙት፡፡
ሜክሲኮ ሰንጋተራ በሚገኘው የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት የዋና ስራ አስፈፃሚው መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የተከናወነው ይህ ስምምነት በእርሻ እና በአግሮፕሮሰሲንግ መስክ ላይ አትኩሮ ለሚሰራው ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ በዘርፉ ለሚያከናውናቸው ተግራት አስፈላጊውን ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እንደያገኝ ያስችለዋል ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ባለሙያዎች ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፕ/ር መንግስቱ ከተማ በበኩላቸው አዲስ እና ትልቅ የሆነ ሀሳብ ይዞ ከመጣው ከፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ጋር ለመስራት መስማማታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ፐርፐዝብላክ ከሙያ ማህበራት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የስራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ሲፈራረም የአሁኑ የመጀመሪያው እና ታሪካዊ ስምምነት መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ፤ እንደ ድርጅት ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በቅርበት የመስራት ፅኑ ፍላጎት አለን፤ በመሆኑም የተፈራረምነው ስምምነት በቀጣይ የምንሰራቸውን ስራዎች በተመለከተ የጋራ ጥናቶችን እንድናደርግ እንዲሁም የግብርናውን መስክ የተመለከቱ የተለያዩ መድረኮችን በጋራ ማዘጋጀት እንድንችል ትልቅ እቅም ይፈጥርልናል የሚል እምነት አለኝ ብለዋል፡፡
ሪፖርተር፡- ናታን ታደለ

 

Leave a Reply

1 × 5 =

×