ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የከገበሬው ምርት ስርጭት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር አካሄደ፡፡

የከገበሬው ምርት ስርጭት ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በኩባንያው ዋና መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ እና ሌሎች የኩባንያው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ጥቅምት 22 ቀን 2015ዓ.ም አከናውኗል፡፡
በመርሀ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ እለቱ ታሪካዊ እንደሆነ ገልጸው የጥቁር ህዝቦችን ታሪክ ዘላቂ በሆነ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመገንባት ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡አክለውም በከገበሬው ምርት ስርጭት ፕሮጀክት የስራ ዕድል ያገኙ ወጣቶች ከፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በታማኝነት ከሰሩ እድገትን ማስመዝገብ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ዓላማ አብሮ በመስራት ድህነትን ታሪክ ማድረግ ነው ያሉት ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ይህ በሚሆንበት ወቅትም አብረን በጋራ ማደግ እንደሚቻል ኩባንያው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸው ተግባራት ማሳያ ይሆናሉ ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ሪቫን በመቁረጥ በይፋ የፕሮጀክቱን ሥራ ያስጀመሩ ሲሆን በእለቱ የተገኙት እንግዶችም ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ከገበሬው ቀጥታ ተረክቦ ከሚያመጣቸው የግብርና ምርቶች በተጨማሪ በኩባንያው እሴት ተጨምሮባቸው የተመረቱ እንደ ዳቦ፣ ሽሮ፣ በርበሬ እና ሌሎች የምግብ ውጤቶች ሸመታ ተካሄዷል፡፡

ሪፖርተር:- ህይወት ከሊል

 

Leave a Reply

1 × 1 =

×