ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች አ.ማ በበቆጂ ከተማ ግዙፍ የተባለውን የሜካናይዜሽን እና ሎጄስቲክ ሰርቪስ ሊሰራ መሆኑ ተገለፀ።

ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች አ.ማ በበቆጂ ከተማ ግዙፍ የተባለውን የሜካናይዜሽን እና ሎጄስቲክ ሰርቪስ ሊሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ይህን የገለፁት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ግንቦት14 2014 ዓ.ም በአርሲ ዞን በቆጂ ከተማ ሊሙ ቡሪቅቱ ቀበሌ ተገኝቶ ከገበሬዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

ፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ በአርሲ ዞን በቆጂ ከተማ ሊሙ ቡርቂቱ ቀበሌ ከሚገኙ ገበሬዎች ጋር ሰፊ ውይይት አካሄደ።

በውይይቱም ስለኩባንያው ገለፃ ያደረጉት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ
ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ በእርሻ ሜካናይዜሽን በምትታወቀው በአርሲ ዞን በበቆጂ ከተማ ግዙፍ የተባለውን የሜካናይዜሽን እና ሎጄስቲክ ሰርቪስ ሊሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚ አክለውም ገበሬውችን በአካል አግኝተው ውይይት በማድረጋቸው ደስተኛ እንደሆኑ ገልፀው የበቆጂ አካባቢ ህብረተሰቦች ለሳዩዋቸው ፍቅርም አመስግነዋል።

የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዓላማ ሸማቹን ህብረተሰብ ከገበሬው ቀጥታ ማገናኘት መሆኑን የጠቀሱት ዋና ስራ ስራ አስፈጻሚው ገበሬው የልፋቱን ውጤት እንዲያገኝ በሁሉም ቦታዎች ላይ በእንደዚ መልኩ መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ ተናግረዋል።

በበቆጂ ከተማ ከሚገኘው የበቆጂ እርሻ ልማት 371 ሄክታር የእርሻ መሬት 80 ሄክታር መሬቱ መልማቱን ያስታወቁት የፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ክንፈ ዘውዴ ይህም ከፐርፐዝ ብላክ ሼር ለገዙ አባላትን የምስራች ይሆናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ፐርፐዝብላክ ሚዲያ በስፍራው ተገኝቶ ያነጋገራቸው በበቆጂ ከተማ የሊሙ ቡሪቂቱ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ገበሬ አቶ ንጉሴ አባቦ እና አቶ ደጀኔ ዘለቀ እንደገለፀት ለብዙ ዓመታት በእርሻ ስራ የቆዩ ቢሆንም የገበያ እጦት ግን ወደ ኋላ አስቀርቷቸው እንደነበር ገልፀው፤ ፐርፐዝብላክ ወደ አካባቢያቸው በመምጣቱ ይህ ችግራቸው ይቀርፍልናል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ገበሬውን ተሳታፊ እና ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ በምናመርተው ምርት ላይ ባለሙሉ ስልጣን ኖሮን በበቂ ሁኔታ ምርታችንን ወደ ህብረተሰቡ እናደርሳለን ለዚህም አብረን ለመስራት በሙሉ ፍቃድ ደስተኛ ሆነው አክሲዮን መገዛታቸውንም ተናግረዋል።
አክለውም ሁሉም ሰው አክሲዮን በመግዛት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች አባል ሆኖ አብሮ በመስራት ተጠቃሚ መሆን እንዲችል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በህይወት ከሊል
ግንቦት 14/ 2014ዓ.ም

Leave a Reply

4 × 3 =

×