ፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከክፍለ ከተማና ከወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ፐርፐዝ ብላክ ኢቲ. ኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊዎች ጋር አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ 11 ክፍለከተሞች እና 10 ወረዳዎች ከተውጣጡየስራ ሀላፊዎች  መክሯል ፡፡

በመድረኩ የፐርፐዝ ብላክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሀ እሸቱ (ዶ/ር) ፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች ትሬዲንግ አ.ማ የተቋቋመበትን ዋና አላማ አስረድተው ኩባንያው በተቋቋመ ጥቂት ወራት ዉስጥ  በግብርና  ፣በሪቴል፣ በግብርና ምርት ማቀናነባበር ላይና ኢ-ኮሜርስ የተሰኘ የበይነ መረብ የግብይት ስርዓትን በመዘርጋት በማይታመን ፍጥነት ዉጤታማ የሆኑ ስራዎችን ማሳለጡን አብራርተዋል ፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚዉ አክለዉም ኩባንያዉ በመላዉ ሀገሪቱ ስራዎችን እያስፋፋ እንደሚገኝና አሁን ላይ በአማራ ክልል (ባህር ዳር)፣ በኦሮሚያ ክልል (አርሲ ዞን ) ፣ በደቡብ ክልል( አርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶና ኦሞ ) ላይ ስራዎችን በማሳለጥ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዉ በመዲናችን አዲስ አበባ ላይ ደግሞ ዋና መቀመጫዉን በማድረግ  ከገበሬዉ በሚል ስያሜ 6 ሱቆች መክፈቱን ተናግረዋል ፡፡

በተጨማሪም በከተማዋ ዜጎች  በቀላሉ ከገበሬዉ ምርትን በቅናሽ  ዋጋ  እንዲያገኙ ለማስቻል በመኖሪያ ስፍራዎች አካባቢ በመኪና ምርትን የማከፋፈል  ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታዉሰዋል ፡፡

በመንግስት በኩል  የተጀመረዉ  እሁድ ገበያ  ከፐርፐዝ ብላክ ዓላማ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ  በመሆኑ  ሀሳብን በመደገፍ በቀጥታ ከገበሬዉ ምርትን ለህብረተሰቡ እያደረሱ መሆናቸዉንና የኑሮ ዉድነትን በማረጋጋት ረገድ ለዉጥ የታየበት መሆኑን አስረድተዉ የመንግስትና የግል ተቋማት በመናበብና በጋራ መስራት አስፈላጊነት ምሳሌም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

መሬት ገፍቶ ህዝብ እየመገበ የሚገኘዉ አርሶ አደር ዛሬም ጎተራዉ የማይሞላበት ምክንያት ከዓመት እስከ ዓመት ለፍቶ ሰብል ከሰበሰበ በኋላ የለፋበት ስራ በግብዞች ሲነጠቅ ማየትም ሆነ ከዕለት ዕለት የሸቀጦች ዋጋ ማነር የኑሮ ምስቅልቅል ዉስጥ የከተተዉን ማህበረሰብ ማየት የሚያስቆጭ መሆኑን የገለፁት የፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች ቴክኒካል ኦፕሬሽን ኦፌሰርና የአግሮ ፕሮሰሲንግ ዲፓርትመንት ሀላፌ ፕ/ሮ ሽመልስ አድማሱ ኩባንያዉ ከመንግስታዊ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት በሚያደርገዉ ጥረት የመንግስታዊ አካላት ቀና ትብብር ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዉ እስከ አሁን መንግስት ለኩባንያ እያደረገ ላለዉ ትብብርም አመስግነዋል ፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉት የክፍለ ከተማ አስተዳደሮችም ፐርፐዝ ብላክ ኢቲ.ኤች ዛሬን ብቻ ሳይሆን እሩቅ አልሞ ለትዉልድ የሚተርፍ ዘመን ተሻጋሪ ሀሳብ ይዞ መምጣቱን አድንቀዉ ዓላማዉ መንግስት ከያዙ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽንና ኢንደስትሪ መር ኢኮኖሚ የሚደግፍ በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል ሲሉ አጋርነታቸዉን አሳይተዋል፡፡

Leave a Reply

14 − seven =

×