በመርሀግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች አ.ማ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጨቆነ ሳይሆን የተከበረ ጥቁር ማህበረሰብ ለማየት ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ማምጣት አማራጭ የሌለው ጎዳይ መሆኑን በማመን የተነሳ ኩባንያ ነው ብለዋል። ቀደምት አባቶቻችን ትውልድ ለማዳንና የተከበረች ሀገር ለመገንባት የደምና የላብ ዋጋ ከፍለው በታላቅ ወኔ ድል አድርገው ሉዓላዊት ሀገር ያቆዮልን […]