ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ በ2015 ዓ.ም የ5000 ሄክታር መሬት ባለቤት ለመሆን እየሠራ እንደሚገኝ አስታወቀ።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ በፍራንቻይዝ ሼር ሆልደር ሞዴል አሁን ላይ ካለው 2200 ሄክታር የእርሻ መሬት በተጨማሪ በዘንድሮ ዓመት የ2800 ሄክታር የእርሻ መሬት ባለቤት ለመሆን አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የኩባንያው ቺፍ ቴክኒካል ኦፕሬሼን ኦፊሰር አቶ ታደለ ሰይፉ ከፐርፐዝብላክ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል። ፐርፐዝብላክ አሁን ላይ በደቡብ ኦሞ ዞን ኒያንጋቶም ወረዳ ከሚገኘው የዶግሞቴ ፋርምስ ፣ በኦሮሚያ ክልል […]

የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ቺፍ ሪቴል ዲስትሪቢዩሽን ኦፊሰር የከገበሬው ሪቴል መደብሮችን የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ከሠራተኞቹ ጋር ውይይት አካሄዱ።

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አ.ማ የከገበሬው ሪቴል መደብሮቹን በተመለከተ እስከአሁን ድረስ ያለውን የሥራ እንቅሰቃሴ በመገምገም በቀጣይ ይበልጥ ውጤታማ ሊያደርገው የሚችለውን ውይይት ቺፍ ሪቴል ዲስትሪቢዩሽን ኦፊሰር ወ/ሮ ሰናይት አየለ፣ አሲስታንት ሪቴል ዲስትሪቢዩሽን ኦፊሰር አቶ አሳየኸኝ እሸቱ እና  የከገበሬው መደብር ሁሉም ቅርንጫፎች የተገኙ ሠራተኞች በተገኙበት ተከናውኗል። በውይይቱ ንግግር ያደረጉት የሪቲል ቺፍ ዲስትሪቢዩሽን ኦፊሰር ወ/ሮ ሰናይት አየለ፤ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ […]

ኤም ኤስ ኤ የተሰኘ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ከፐርፐዝብላክ ኢቲ ኤች የግብርና ምርቶችን ለመውሰድ 3.5 ቢሊዮን ብር ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ የተፈረመው ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች 1ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ነው። ድርጅቱ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር 3.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት የግብርና ውጤቶች እንዲያቀበርብለት መሆኑም ተነግሯል። ክብረ በዓሉ እኔም ገበሬ ነኝ በሚል መሪ ቃል በፐርፐዝብላክ ዋና መስሪያ ቤት የተከወነ ሲሆን የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ከ 250 […]

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነውን ዓለም አቀፍ ታላቁ ሩጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገለፀ ፡፡

ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር አንድነት ርሃብን ለማስቆም በሚል መሪ ቃል የዓለም ታላቁ ሩጫ ውድድር ለማዘጋጀት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አሳውቋል ፡፡መዝናኛን ለቁም ነገር ፤ አንድነት ርሃብን ለማስቆም የዓለም ታላቁ ሩጫ ውድድር እየተዝናኑ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በዘላቂነት መደገፍ የሚችሉብት ነውም ተብሏል ፡፡ውድድሩን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ፍ ፍሰሃ እሸቱ […]

×