የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ እና በደቡብ ኦሞ ዞን ኒያንጋቶም ወረዳ የሚገኘው የአስቴር ተፈራ ግብርና ልማት ማህበር ባለቤት ወ/ሮ አስቴር ተፈራ አብሮ መስራት የሚያስችላቸውን የስራ ውል ስምምነት ሰነድ አዲስአበባ በሚገኘው የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ፤የካቲት28 ቀን 2014 ዓ.ም ተፈራርመዋል። በዚሁ ስምምነት ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች 8መቶ ሄክታሩ መሬቱን በእርሻ በፍራንቻይዝ ለዲያስፖራዎችና ለኢንቨስተሮች ጨምሮ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በአንድ መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር ጀምሮ ለሼር ሸያጭ አቅርቧል፡፡ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች የጀመረው የፍራንቻይዝ ሼር ሆልደር ሞዴል ዋናው ሀሳብ፣ አቅም ያላቸው ሰዎች አብረው የሚሰሩበትን መድረክ መፍጥር መሆኑን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው በ ደቡብ ኦሞ ዞን ኒያንጋቶም ወረዳ ከሚገኘው የአስቴር ግብርና ልማት ባለቤት ወ/ሮ አስቴር ተፈራ እና የእርሻ ስፍራ ምቹ መስረተ ልማቶችን ያሟላ በመሆኑ ውጤታማ መሆን እንደሚያስችላቸው በስምምነቱ ወቅት ገልፅዋል።
ሀገራችን ካላት ሀብት የሚገባትን ያህል መጠቀም አልቻለችም ያሉት የአስቴር ተፈራ ግብርና ልማት ማህበር ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ሲኔቦ ከፐርፐዝብላክ ጋር መስራት መጀመራቸው የረጅም ግዜ ቁጭታቸውን ወደ ውጤት ለመቀየር ትልቅ አጋጣሚ እንደሚፈጥርላቸው ተናግሯል። የፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ የአስቴር ግብርና ልማት ከ ድርጅታቸው ጋር አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ ሆኖ በመምጣቱ ምስጋቸውን አቅርበው፤ በቀጣይ አመርቂ ውጤት ለማምጣት አብረው እንደሚሰሩም ገልፀዋል። ፐርፐዝብላክ ኢቲ ኤች ትሬዲንግ አ.ማ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ በደቡብ ኦሞ ዞን ኒያንጋቶም ወረዳ ከሚገኘው ከዶግሞቴ እርሻ ጋር በእርሻ ፍራንቻይዝ ሼር ሆልደር ሞዴል አብሮ ለመስራት ተስማምቶ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወስ ነው።
Leave a Reply